
የፍሊንትስቶን ኢንጂነሪንግ አክሲዮን ማህበር 8ተኛው መደበኛ እና የመጀመሪያው ህዝባዊ ጠቅላላ ጉባኤ
ኩባንያችን ፍሊንትስቶን ኢንጂነሪንግ አክሲዮን ማህበር ከተመሰረተ ሶስት አስርት አመታት ያለፈው ሲሆን ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ቤተሰባዊ የነበረው እና በሰባት ባለአክሲዮኖች ባለቤትነት ብቻ ሲመራ የነበረውን አደረጃጀቱን ህዝባዊ ለማድረግ በመወሰን የአክሲዮኖቹን ሽያጭ ለህዝብ ክፍት አድርጓል። በዚህም መሰረት ህዝባዊ ከሆነ የመጀመሪያው የሆነውን ጠቅላላ ጉባኤ ታህሳስ 12 ቀን 2017 ዓ.ም በጊዮን ሆቴል በተሳካ ሁኔታ አካሂዷል። ታህሳስ 12 ቀን 2017 ዓ.ም ባካሄድነው የኩባንያችን ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ከ300 በላይ ባለአክሲዮኖች የተገኙ ሲሆን ኩባንያችን የፋናንስ አፈጻጸም ሪፓርቱን ለባለ አክስዮኖች ይፋ አድርጔል:: በበጀት ዓመቱ ያስመዘገብነውን አጠቃላይ ገቢ 829 ሚሊየን 253 ሺህ 092 ብር እና ; ከታክስ በፊት ያተረፍነው ያስመዘገብነው ጠቅላላ ትርፍ 36 ሚሊዮን 658 ሺህ 747 ብር መሆኑን በጉባኤው አሳውቀናል። ይህም ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ከነበረን ትርፍ ጋር ሲነፃፀር 84 በመቶ እድገት ማሳየቱን የዳይሬክተሮች ቦርድ ሪፖርታችን ያሳያል። በተጨማሪም የኩባንያችን የተጣራ ትርፉ 25 ሚሊዮን 61 ሺህ 865 ብር ሲሆን በአንድ አክሲዮን ላይ የተገኘ ትርፍ 33.62 ብር ሆኖ ተመዝግቧል ።የባለአክሲዮኖችን ቁጥርም ከ7 ወደ 1 ሺህ 799 አሳድገናል:: የሙሉ ቀን ጠቅላላ ጉባኤ በተጨማሪም በዕለቱ ከአንድ ጠቅላላ ጉባኤ የሚጠበቁት ህጋዊ ዋና ዋና ተግባራት ያከናወንን ቢሆንም በልዩ ሁኔታ ከባለአክሲዮኖች ጋር ሰፊ ውይይት ለማድረግ የከሰአት ውይይት መድረክ አዘጋጅተን ባለአክሲዮኖች ድርጅታቸውን በደንብ እንዲያውቁ፣ ዝቅተኛ ቁጥር ያለው የአክሲዮን ድርሻ የገዙ ባለአሲዮኖች መብት እና ሚና ላይ እንዲሁም ኩባንያችን የሚያጋጥመውን ተግዳሮቶች እና የድርጅቱ ህልሞች ላይ ሰፊ ውይይት አከናውነናል። በውይይቱም ላይ የኩባንያችን ባለአክሲዮኖች ተጨማሪ ጥያቄዎችን ያቀረቡ ሲሆን ሰፊ ውይይት እና ግብአት መሰብሰብ ተከናውኖባቸዋል። ጠቅላላ ጉባኤው በአይነቱ የተለየ የሆነበት ምክንያት የመጀመሪያው የኩባንያችን አደረጃጃት ሙሉ ለሙሉ ከግል ወደ ህዝባዊ የተሸጋገረበት የመጀመሪያው መሆኑ ሲሆን ከመነሻው በብዙ ሰው አማካኝነት ከሚደራጁ ድርጅቶች በጣም ለየት ያደርገዋል። ሁለተኛው ያልተለመደው የሙሉ ቀን ውይይት ማካሄድ እና ከባለአክሲዮኖች ጋር ሰፊ እና ግልጽ ውይይት የማድረጊያ እድል መክፈቱ ሲሆን ባለአክሲዮኖችም ይህንን የግልጽነት እና አሳታፊነት አሰራር አበረታትተዋል። የስራ አመራር ቦርድ አባላትም ኩባንያችን የሚታወቅበትን አዳዲስ ልምዶችን ማስተዋወቅን እንደሚቀጥሉበት ከባለአክሲዮኖች ጋርም ጠበቅ ያለ ግንኙነት አንዲኖር እንደሚሰሩ ማረጋገጫ ሰጥተዋል።