//የፍሊንትስቶን መተግበሪያ ሰብስክሪብሽን ልዩ ሽልማት
የፍሊንትስቶን መተግበሪያ ሰብስክሪብሽን ልዩ ሽልማት

የፍሊንትስቶን መተግበሪያ ሰብስክሪብሽን ልዩ ሽልማት

የፍሊንትስቶን መተግበሪያ ሰብስክሪብሽን ሎተሪ ፕሮሞሽን ከሚያዚያ 16 2016አ.ም እስከ ነሃሴ 19 2016አ.ም ድረስ የተደረገ የመተግበሪያ ማስተዋወቂያ ሲሆን የዚህ የሽልማት ፕሮሞሽን አላማው ፍሊንትስቶን ኢንጂነሪንግ በጥር ወር 2016 አ.ም ላይ ወደ አገልግሎት ያስገባው መተገበሪያን ማስተዋወቅ እና የፍሊንትስቶንን ቤተሰቦችን ማበረታት ነው :: መተግበሪያው በአሁኑ ሰዓት አጠቃላይ የተመዘገቡ 27,000 (ሃያ ሰባት ሺህ) ብስክራይበሮች ያሉት ሲሆን በዋናነት የፍሊንትስቶንን አክሲዮን ካሉበት ሆነው መግዛት የሚችሉበት ፣ባለ አክሲዮኖች ቀሪ ክፍያቸውንም በመከታተል የሚከፍሉበት ፣ዲጂታል የአክሲዮን ሰርተፊኬት ማረጋገጫ የሚወስዱበት ፣ስለኩባንያው መሰረታዊ መረጃዎች የሚገኙበት ነው:: በጥቅምት 27 ቀን 2017 አ.ም በብሄራዊ ሎተሪ አገልግሎት በይፋ በወጣው የእጣ ማውጣት ስነስርአት 15 ባለ ዕድለኞች ዕጣው ውጥቶላቸው በዋና ቢሮ በታህሳስ 26 ቀን 2017 አ.ም በመገኘት ሽልማታቸውን ተረክበዋል:: ሽልማቱ በዕጣው ብዙ አይነት ሽልማቶች የተካተቱ ሲሆን ባለ ዕድለኞች ከቤት እድሳት ጀምሮ ፣ የጉዞ እና የሆቴል ፓኬጅ ፣ የጂም የአንድ አመት ጥቅል ፣ ስማርት ስልኮች እንዲሁም የተለያዩ ልዩ ልዩ ሽልማቶችን ተሸላሚ ሆነዋል። የፍሊንትስቶን ሽልማት ዕጣ ውስጥ በመጀመሪያው ዕጣ የቤት እድሳት የባለ ዕድለኛው ቤት በልዩ ሁኔታ እድሳት ሚሰራለት ይሆናል። ቤት ሁሉም ሰው እቅድ ውስጥ ያለ ነገር በመሆኑ የመጀመሪያውን እጣ እጅግ ተፈላጊ ያደርገዋል። ፍሊንትስቶን በቀጣይም ይህንን ቤትን አድሶ የማዘመን ስራዎች በስፋት የሚሰራ ይሆናል፡፡ ወደፊትም ፍሊንትስቶን በተለያዩ መንገድ ቤተሰብ የሚሆኑትን ልዩ ልዩ ሽልማቶች መሸለሙን ሚቀጥል ይሆናል የማህበራዊ ገፅ ተከታዮቹን የአፕሊኬሽን ሰብስክራይበሮቹን ለማበረታታት በአይነትም በብዛትም ከፍ ያሉ ሽልማቶች ለመሸለም ታቅዷል።

ተዛማጅ ዜናዎች

የፍሊንትስቶን መተግበሪያ ሰብስክሪብሽን ልዩ ሽልማት / ፍሊንትስቶን ሆምስ