Meeting with home owners


በሀርመኒ ሆቴል ተከታታይ አምስት ቀናት በፍሊንስትስቶን ቤቶች ፕሮጀክቶች የተመረጡ ስድስት ፕሮጀክቶችን በልዩ ልዩ አጀንዳዎች እና በአሁኑ ጊዜ በተከሰተው የኢኮኖሚ አለመረጋጋት በፕሮጀክቶቹ እንቅስቃሴ ላይ በተለይም የውጭ ምንዛሬን እና የአርማታ ብረት ከገበያው መጥፋት በተመመከተ ከደንበኞች ጋር በመወያየት ቀጣዩን ሂደት አብሮ በማቀድ ግልጽ እና ጠቃሚ ውይይት ተካሂድ ነበር ፡፡ በሁለም ውይይቶች ተሳታፊዎች እና የፍሊንትስቶን አመራሮች ስምምነት የተደረሰበት ጉዳይ ባለፉት ወራት በነበረው የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ አለመረጋጋት እነዚህ ፕሮጀክቶች በጊዜ እና በገንዘብ ተጎድተዋል፡፡

በተጨማሪም ደንበኞች ከሞላ ጎደል በአጠቃላይ ይህ ሁኔታ ከአልሚው ከፍሊንትስቶን ቁጥጥር ውጪ የተከሰተ አስቀድሞ ሊገምተውም ሊጠብቀውም የማይችል መሆኑን ተስማምተዋል፡፡ አንድ አንድ ተሳታፊ ደንበኞች በባከነው ጊዜ እና በደረሰው ፋይናንሻል ጉዳት እንደ አስተያየት አድርገው የኮንትራቱ ጊዜ እና ዋጋ ማስተካከሌ ፤የተሻለ የገበያ ሁኔታ ቁጭ ብል በመጠበቅ ከሚደርስ ተጨማሪ ጉዲት የተሻለ አማራጭ ነው ብለዋል፡፡ ምንም ይህ ሀሳብ በአመዛኙ ከተሳታፊዎች በተደጋጋሚ የቀረበ ቢሆንም በፍሊንስቶን በኩል ከዚህ በተቃራኒው 


1. በኮንትራቱ መሰረት ከዋጋ ጭማሪ ደንበኞች ውል ላይ በተጠቀሰው አንቀጽ የተጠበቁ መሆኑን 


2. የፕሮጀክቶች የፋይናንሻል ስጋት/ financial risk /ዋስትናው የሚረጋገጠው በየፕሮጀክቱ ሳይሸጡ በሚቆዩ ቤቶች እና ሱቆች ሪዘርፍ ዩኒት መሆኑን እነዚህም ገበያውን ተመልሰን ሲረጋጋ ጉዳቱን በሚያካክስ ዋጋ እንዲሚሸጡ ይኽም የፕሮጀክቶቹን የፋይናንሻል ስጋት እንደሚስተካከል አስረድተዋል ፡፡


 በተጨማሪም  የተነሳ ሀሳብ ደንበኞች ፕሮጀክቱን የማገዝ ፍላጎት በዚህ ብቻ የተገደበ አልነበረም ደንበኞች በዚህ ባልተረጋጋ ጊዜ ውስጥ የፕሮጀክቶቹ የገንዘብ ዕጥረት ያጋጥማቸዋል ብሎ በመገመት የገንዘብ እጥረታቸውን አስቀድሞ ክፍያዎችን የመክፈል ሀሳብም ተነስቶ ነበር ሆኖም ይህም ቢሆን ውጤታማ ሊሆን የሚችለው ገበያው ተረጋግቶ አቅርቦቱ ተስተካክሎ ደንበኞች ክፍያ ወይ አርማታ ብረት ወይም ደግሞ ከውጭ የሚገቡ ዕቃዎች በውጭ ምንዛሪ ግብይት የሚውል ከሆነ ብቻ ስለሆነ የኢኮኖሚው መረጋጋቱ የብረት አቅርቦት እና የውጭ ምንዛሬ አቅርቦት መስተካከለ ሲረጋገጥ በፈቃድኝነት ላይ የተመሰረተ አስቀዴሞ የመክፈል ጥያቄ ፍሊንትስቶን ሊያቀርብ እንደሚችሌ ተገልጽዋል፡፡ቀጥሎ የተነሳው አንገብጋቢ ጉዳይ በወቅታዊ ሁኔታው ምክንያት የባከነው ጊዜ ተምኖ በኮንትራቱ የጊዜ ማሻሻያ ጊዜ ማቅረብ የሚለው ነበር ከዚህም ከፍሊንስቶን አመራር የተሰጠው መልስ በአሁኑ ሰዓት


በሚከተሉት ሶስት ጉዳዮች ላይ ፍሊንትስቶን በነጠላም በአንዴነትም የባከነውን ጊዜ በማካካስ ይረዳል ብሎ የወሰናቸውን ተግባራት ሊያከናውኑ ስለሆነ የተጋባራቱ ውጤት የባከነውን ጊዜ ምንያህል እንደሚያካክስ ባልታወቀበት ሁኔታ የጊዜ ማራዘሚያ መጠየቅ ስንፍና እንጂ ጉብዝና ስለማይረዳ የሚከተሉት ሁኔታዎች ሲጠናቀቁ ይህንንም እንደሁኔታው በፍሊንትስቶን የሚጠየቅ መሆኑ ተገልጽዋል ተግባራቱም


1. ከ አዲስ አበባ ስድስት ከ.ሜ ርቀት ላይ ከሚገኝ የኢንዱስትሪ መንደር ዉስጥ በኤሌክትሪክ የሚሰራ አነስተኛ የአርማታ ብረታብረት ማምረቻ ፋብሪካ ለማቋቋም እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛል ፡፡ ይህ እንቅስቃሴ ከሶስት ወር እስከ ስድስት ወር ጊዜ የሚፈጅ ሲሆን የሚጠይቀዉ የካፒታል ኢንቨስትመንት ቀዴሞ ከተሰበሰቡ ገንዘቦች ላይ የተዘጋጀ ስለሆነ በተጨማሪም ለማኒፋክቸሪነግ ኢንዱስትሪ የብድር አቅርቦቱ በቂ እና የተፋጠነ በመሆኑ የመሳካት እዴሉ ከፍተኛ ነዉ፡፡


2. ከአንዴ ትልቅ አቅም ካለዉ የዉጭ ስራ ተቋራጭ ጋር የተጀመረ እያንዳንዱ ፕሮጀክት ላይ የነጠላ ስምምነት በማድረግ ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልገዉን የኮንስትራክሽን አገልግሎት እንዲሁም የአርማታ ብረትና ከዉጭ የሚገቡ  የኮንስትራክሽን ግብይቶችን በደቤ ስምምነት ለማቅረብ በድርድር ሊይ እንገኛለን ፡፡ ይህ ድርድር እስከሚጠናቀቅ ድረስ የድርጅቱ ማንነትና የድርጅቱ ማዕቀፍ መግለጽ ተገቢ አይሆንም ሆኖም ድርድሩ ሲጠናቀቅ የስምምነቱን ማዕቀፍ በየፕሮጀክቱ ለየፕሮጀክቱ ደንበኞቻችን የምናሳዉቅ ይሆናል፡፡ 


3. የገበያዉ አለመረጋጋት የፈጠረዉን እጥረት በመስበር የመንግስት እና ከገበያዉ ዉጭ የሆኑ ነጋዳዎችን ድጋፍ በማስተባበር በፖሊስ ዉጭ እና በህግ ማስከበር የተባበረ ስራ ጊዜአዊ ወይም ቋሚ የአርማታ ብረት አቅርቦትና የዉጭ ምንዛሬ አቅርቦት እንዲስተካከል በማድረግ እና ከሚዲያ እና በማህበራት በመጠቀም የadvocacy ስራ ፍሊንትስቶን እየሰራ መሆኑን አስረድቷል፡፡ በተለይም በጅቡቲ የተከማቸዉ በርካታ የአርማታ ብረት በfranco valuta እንዲገባ እንዲፈቀድ ከማሳሰብ ጀምሮ መንግስት የመንግስት ግዥን ኤጀንሲን በመጠቀም ገበያዉን በማረጋጋት ተመጣጣኝ የሆነ መጠን ያለዉ ምርት እንዲያስገባ እየተማጸንን እንገኛለን ይህንን advocacy ማጠናከርም በአሁኑ ሰአት ለሁሉንም ሁኔታዎች አካቶ(የዉጭ ምንዛሬ ሌዋጭን ጭምር )የአርማታ ብረት ከፋብሪካ ዉስጥ ለማምረት ብር 14 በኪል ግራም ብቻ እንደሚፈጅ ነገር ግን በአንጻሩ በስብሰባዉ ወቅት ብር 50 እንዲረስ በስብሰባዉ ወቅት ተገልጻል (ይህ ቃል ጉባዕ በተዘጋጀበት ሰአት በአንድ አንድ አካባቢዎች የብረት ዋጋ በ65 ከ.ግ መሸጥ ተጀምሯል)እነዚህ ሁለ ጉዳዮች ወደ መሬት ከወረደ በየፕጀክቶች ሚያከናዉኑት ስራዎች ከክፍያ ምዕራፎቹ ጋር (milestone payments) የተገናዘበ ተሸሻሎ እቅድ ማዘጋጀትን እንደሚጠይቅ ስምምነት ላይ ተደርሷል እቅዶቹም ከሞላ ጎደሌ ሁለም ነገሮቹ ቢሳኩ እንደከፍተኛ ግብ ሆኖ (optimistic scenario) ከሞላ ጎደሌ ሁለም ነገር ባይነካ ዝቅተኛ ግብ ሆኖ (pessimistic scenario) ከዛ ደሞ በከፊል ነገሮች ቢሳኩ (most likely scenario) መካከለኛ ግብ ሆኖ እቅድች እንዱዘጋጁ እና ከሶስት ወር ባላነሰ ከስድስት ወር ባልበለጠ ጊዜ ዉስጥ እርግጠኛ የየፕሮጀክቶቹ መጠናቀቂያ ጊዜ እንዲሁም የክፍያ ጥየቄዎች ጊዜዎቹ ተስተካክለዉ ሁሉም ደንበኞች እንደሚገልጽ ስምምነት ላይ ተደርስዋል፡፡ 


በአጠቃላይ በደንበኞች እና የአልሚው ፍሊንትስቶን አመራሮች የተደረገው ውይይት በተከሰተው አለመረጋጋትማንም ተጠያቂ መሆን ባይችልም አልሚው ከአሁኑ ልምድ አንጻር አሁን እንደአማራጭ ያስቀመጣቸው ተግባራት ከዚህ በፈጠነ እና በቀደመ ሁኔታ መፈጸም ይገባዉ እንደነበር በብዙ ተሳታፊዎች በተለይም በየፕሮጀክቶቹ ከተደራጁት የደንበኞች  ማህራት አመራሮች ተገልጸዋል ፡፡ በዚህ አጋጣሚ የደንበኛ ማህበራት መደራጀት የደንበኞችን ጥቅም በተደራጀ መልኩ ማስከበር በተደራጀ መልኩ ማስከበር ዋናዉ ተግባሩ ከመሆን አልፎ ፕሮጀክቶች እንዲሳኩ አመራሩን በማገዝ ሀሳብ  ማፍለቅ እና የደንበኞችን ጥቅም ከግሌ አተያየት ብቻ ሳይሆን ከጋራ ጥቅም አተያየትም እንዲቃኝ በማድረግና ትልቅ አስተዋጽኦ እንዲኖረዉ የተረጋገጠበት መድረክ ነበር፡፡ 


ዋና ተግዳሮት በዚህ የማህበራቱ አስተዋጽኦ ሆኖ የተገኘዉ የአልሚዉ የፍሊንትስቶን ወቅታዊ መረጃ አለማቅረብ ወይም የቀረበዉን በወቅታዊ መረጃ አለማድረስ (update) አለማድረግ እንዲሁም ተገልጸል፡፡ ስለሆነም ከስብሰባዉ ወቅት ጀምሮ በአልሚዉ እና በህዝብ ግንኙነት አጋራችን በማቭሪክ ፕሮሞሽን በተደረገ የራስ ግምገማ (self-assessment)በስብሰባ የተገለጹትን ችግሮቻችንን ለማስተካከል ተንቀሳቅሰን የመጀመሪዉ ዉጤት በዚህ audiovisual እንዱሁም ቅርጽና ይዘቱን አስተካክል በወጣዉ ድህረ ገጻችን ተደርገዋል ፡፡ 


https://www.youtube.com/watch?v=iJqNPvz1nPg&t=9shttps://www.youtube.com/watch?v=-WJzluZjgfU,https://www.youtube.com/watch?v=9z-h148JDns&t=9s,https://www.youtube.com/watch?v=GzIvLEqeJxE,https://www.youtube.com/watch?v=i8-8x__QQCc&t=9s,https://www.youtube.com/watch?v=_Y-dNDu1pzI&t=11s,https://www.youtube.com/watch?v=_52-Bhjln-s&t=9s,https://www.youtube.com/watch?v=6q3VIvJQNy0&t=10s,https://www.youtube.com/watch?v=LTH0oNIxr_I&t=6s,https://www.youtube.com/watch?v=3UYuPYouzyw&t=8s,https://www.youtube.com/watch?v=g4Dgl7gk3Gs&t=61s

ሁሌጊዜም የእናንተ የሆነዉን ፍሊንትስቶን ይዘቱንም ሆነ ቅርጹን በእናንተ በደንበኞች አስተያየት እያሻሻልን ሁሌጊዜም ፍሊንትስቶን የእናንተ እንደሆነ እንዲቀጥል እንሰራለን፡፡ 

Subscribe for updates

Subscribe for updates about Flintstone Homes, get notification for new offers and promotions.

Find us on Social Media