Flintstone logo
  • Home
  • Projects
  • About Us
  • Begara
  • Contact Us
  • የፍሊንትስቶን ኢንጂነሪንግ አ.ማ

    የምዝገባ ቅጽ

    1. መግቢያ

    የፍሊንትስቶን ኢንጂነሪንግ አክሲዮን ማህበር ከዚህ በፊት የነበረውን የፕሮጀክት አስተዳደርን ከገዥ ደንበኞች ጋር በጋራ ማድረግን በማስፋት የፕሮጄክት ቁጥጥርን ለማጠናከር ቤት ገዥዎችን ከፕሮጄክቱ መነሻ ጀምሮ አደራጅቶ በጋራ ለመስራት ይፈልጋል።

    2. የፕሮጀክቱ አጠቃላይ መግለጫ

    በዚህም መሰረት ይህንን ቅጽ የሚሞሉ የወደፊት ደንበኞች ፍላጎታቸውን መሰረት በማድረግ ከ 12- 25 ቤቶች የሚኖሩት የጋራ ህንጻ ላይ ቤት የሚገዙ ሲሆን በህንጻው ላይ ቤት የገዙ ደንበኞች ጋር በጋራ ማህበር በመመስረት የፕሮጄክቱን ሂደት ከመነሻው እስከማጠናቀቂያያ የሚቆጣጠሩ እና የሚያሰሩ ይሆናል። ስራው ሲጠናቀቅም ንብረታቸው ያስተዳድራሉ።

    3. ደንበኞች ቤታቸውን እንዴት ገዝተው እንዴት ይሰራል?

    3.1 የመጀመሪያ ምዝገባ

    • ደንበኞች መስፈርቱን አሟልተው አስፈላጊውን ቅጽ በግንባር ወይም ኦንላየን ይሞላሉ።

    3.2 የቦታ ምርጫ

    • ቅጹን ከሞሉ በኋላ ባሉት 60 ቀናት ውስጥ ካሉት የፕሮጄክት ሳይቶች መካከል ይመርጣሉ።
    • በቅደም ተከተል ሶስት ምርጫዎቻቸውን ያሳውቃሉ።
    • ከረጡ በኋላ ባሉት 10 ቀናት ውስጥ በቀረበላቸው ምርጫ ከተስማሙ በገዥዎች አብረው ሳይቱ ላይ የሚገዙትን ሰው ይተዋወቃሉ፣ የተናጠል የቤት ግዥ ውል ይፈርማሉ።

    3.3 ክፍያ እና አደረጃጀት

    • የመጀመሪያ ክፍያውን ሲፒኦ አሰርተው ያመጣል፣
    • በፕሮጄክት ሳይቱ ላይ 50 በመቶ የደንበኞች ቁጥር ወይም ከዚያ በላይ ሲሟላ የደንበኞች የቁጥጥር ኮሚቴ ይመረጣል።
    • በሳይቱ ላይ ያሉ የደንበኞች የጋራ መግባቢያ ሰነድ ይፈረማል።
    • ከ50 በመቶ ደንበኞች በኋላ የሚጨመሩ ደንበኞች የጋራ መግባቢያ ሰነዱን በመፈረም ፕሮጄክቱን ይቀላቀላሉ።
    • በደንበኞች የቁጥጥር ኮሚቴ እና በድርጅቱ የፕሮጄክት አስተዳደር የሚፈረም የጋራ አካውንት ይከፈታል።
    • የሁሉም ደንበኞች ክፍያ በዚህ አካውንት ውስጥ ይገባል።

    3.4 ግንባታ እና ርክክብ

    • ፍሊንትስቶን ፕሮጄክቱን ያስጀምራል፣ የደንኞች ኮሚቴ ስራውን ይቆጣጠራል።
    • ደንበኞች እስከ በሁለት አመት ባለው ጊዜ ውስጥ ቤታቸውን ይረከባሉ።
    • የደንበኞች ቁጥጥር አደረጃጀት ወደ ነዋሪዎች ማህበር ይቀየራል።
    • ለዚህ ሂደትም ፍሊንትስቶን ማንኛውንም ድጋፍ ያደርጋል።

    4. የመመዝገቢያ መስፈርቶች

    4.1 የንብረት መስፈርቶች

    • ከ 12- 25 ሰው የሚኖርበት የጋራ ህንጻ ላይ ቤት የመግዛት ፍላጎት ያለው/ያላት
    • ከ 4 ሚልዮን ብር ጀምሮ የሚያወጣ በከፊል የተጠናቀቀ አፓርታማ ቤት የመግዛት አቅም ያለው/ያላት

    4.2 ሌሎች መስፈርቶች

    • በገዥዎች ጋር በጋራ ለመደራጀት ፍቃደኛ የሆነ/የሆነች
    • ይህንን የምዝገባ ቅጽ በመሙላት ውል ሲፈረም የሚታሰብ 10 ሺህ ብር የከፈለ/የከፈለች
    • ይህንን ቅጽ በሚሞላበት ወቅት የሶስት ወር የባንክ እንቅስቃሴው/ዋ ውስጥ 300 ሺህ ብር ድረስ አካውንቱ/ቷ ውስጥ ማሳየት የሚችል/የምትችል

    5. የምዝገባ ቅጽ መሙላት

    ከዚህ ቅጽ ጋር የተመዝጋቢው የባለፉት 3 ወራት የባንክ እንቅስቃሴ 300 ሺህ መሆኑን የሚያሳይ የሂሳብ መግለጫ እና የመመዝቢያ 10 ሺህ ብር የተከፈለበት ማስረጃ አብሮ መያያዝ አለበት። ከምዝገባው ስሙ እንዲሰረዝ የፈለገ ሰው ጥያቄውን በጽሁፍ ባቀረበ ወቅት ገንዘቡ ወደ አካውንቱ የሚመለስለት ይሆናል።

Flintstone Homes LogoBole homes, on the road from Bole homes to Korea hospital+251-910-903-131 / 8188 (Quick Call)flintstonehomes@gmail.com

Quick Links

  • Featured Blogs
  • Featured News
  • FAQ
  • Properties
  • Our Journey
  • Team

Social Media

© 2025 Flintstone Homes. All rights reserved.