
ፍሊንትስቶን ሆምስ በመሃል ከተማ ቤቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ለሽያጭ አወጣ
ከፍሊን ትስቶን ሳይቶች መካከል አርባ ደረጃ እና ካዛንቺስ የመኖርያ መንደሮች አካባቢያቸው ውብ፣ አረንጏዴ፣ ሰፊ የመዝናኛ ስፍራ እና የጋራ መጠቀሚያ የበዛባቸው መሆናቸው ለመኖሪያ ተመራጭ አድርጏቸዋል :: አርባ ደርጃ ራስ መኮንን ድልድይ ናዝሬት ት/ቤት ፊት ለፊት ሲገኝ ካዛንቺስ የመኖርያ መንደር ደግሞ ሴቶች አደባባይ እንደራሴ ሜዳ ፊት ለፊት ይገኛል:: ሁለቱም ሳይቶች መገኛቸው መሃል ከተማ መሆኑ እና በይበልጥም አካባቢያቸው ላይ በተከናወነው መሰረተ ልማት በደንበኞች እጅግ ተመራጭ እና ተወዳጅ እየሆኑ መጥተዋል:: በተጨማሪም የሳይቶቹ የግንባታ ሂደት እንዲሁም የደንበኞች ተዋውቀው እና ተደራጅተው ለሳይቱ ግንባታ ፍጥነት መተባበር/ መንቀሳቀስ ሳይቱን ከታሰበለት የርክክብ ቀን የሚያስቀድመው ሲሆን በወጣለት ፕሮግራም እንደአዋሬ እና ካዛንቺስ 1 ሳይቶች በቅርብ ወደነዋሪ ይሸጋገራሉ ተብለው እየተሰሩ ካሉ ፕሮጀክቶች ቀዳሚ ናቸው:: ፍሊንትስቶን ለሳይት ጉብኝት ከቢሮ መኪና እና ባለሞያ መድቦ ፍላጎት ያላቸውን ደንበኞች የሚያስጎበኝ ሲሆን በእነዚህ በሁለት ሳይቶች በጣት የሚቆጠሩ ቀሪ ቤቶች ለሽያጭ ስለወጡ በቀጥታ ወደ ሳይቱ በመሄድ እንዲመለከትዋቸው ደንበኞችን ይጋብዛል:: በአርባ ደረጃ 4 ቤቶች እና በካዛንቺስ 3 ቤቶች ብቻ የሚገኙ ሲሆን ደንበኞች ቅድመ ክፍያ 30 በመቶ ከፍለው ቀሪውን በሁለት አይነት አከፋፈል የሚስተናገዱ ይሆናል:: ቀድመው በመደወል ሳይት ይጎብኙ ይግዙ ለተጨማሪ መረጃ በ8188 ይደውሉ ::