የፍሊንትስቶን ኢንጂነሪንግ አክሲዮን ማህበር የደንብና ሁኔታዎች አጭር መግለጫ  


1.

የፍሊንትስቶን ኢንጂነሪንግ አክሲዮን ማህበር አክዮኖች ሽያጭ በንግድ ህግ አዋጅ ቁጥር 1243/2013 መሰረት ነዉ፡፡


2.

የአክሲዮኖች ዋጋ
  • የአንድ መደበኛ አክሲዮን የተጻፈ ዋጋ (ፓር ቫልዩ) – 500 ብር
  • የአንድ መደበኛ አክሲዮን የዋጋ ብልጫ (ፕሪሚየም) – 250 ብር
  • መግዛት የሚቻለው ዝቅተኛ የመደበኛ አክሲዮን ብዛት - 100 አክሲዮኖች
  • መግዛት የሚቻለው ከፍተኛ አክሲዮን ብዛት - 4000 አክሲዮኖች

3.

የአክሲዮን ግዥ መፈጸም የሚቻለው በባንክ ወይም በፍሊንትስቶን ዲጂታል መተግቢያዎች ብቻ ሲሆን በጥሬ ገንዘብ ልውውጥ ሽያጭ አይፈጸምም።


4.

አክሲዮኖቹ ለማንኛውም ግለሰብ ህግን በተከተለ መልኩ መተላለፍ ይችላሉ።


5.

በዲጂታል መንገድ ግዥ የሚፈጽሙ ደንበኞች እስከሁለት አመት ድረስ በተራዘመ ክፍያ ግዥ መፈጸም ይችላሉ። ዝቅተኛ የተራዘመ ክፍያ መጠን የአንድ አክሲዮን ዋጋ ነው፡፡


6.

የባለአክሲዮንነት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት የሚሰጠው ሙሉ ክፍያ ከፍለው ላጠናቀቁ ደንበኞች ብቻ ነው፡፡


7.

በዲጂታል መንገድ አክሲዮን የሚገዙ ደንበኞች የአገልግሎት ክፍያ አይከፍሉም፣ ክፍያቸውን ሲያጠናቅቁም የአንድ አክሲዮን ዋጋ ተመላሽ ይሆንላቸዋል።


8.

በዲጂታል መንገድ ግዥ በመፈጸም በአንድ ጊዜ ክፍያ አክሲዮኖችን ከፍለው ያጠናቀቁ ደንበኞች የ10 በመቶ ቅናሽ በተመላሽ የሚያገኙ ይሆናል።


9.

የአክሲዮን ባለድርሻዎች በጽሁፍ ጥያቄ አቅርበው በዳይሬክተሮች ቦርድ ከተፈቀደ በኋላ አክሲዮኖችን ሙሉ ወይም ከፊል ድርሻን ወደቤት ግዥ ማዞር ይችላሉ።


በንግድ ህግ አዋጅ ቁጥር 1243/2013 መሰረት ደንብ እና ሁኔታዎች ተፈጻሚነት አላቸው፡፡