ዛሬውኑ ይመዝገቡ


በአነስተኛ ካፒታል በፀደቀ ይሁኔ ወልዱ ተመስርቶ ከሰላሳ አመታት በላይ በኮንስትራክሽን እና በሪልስቴት ዘርፍ ጉልህ ተሳትፎ እያደረገ የሚገኘው ፍሊንትስቶን ኢንጅነሪንግ (በብራንድ ስሙ ፍሊንትስቶን ሆምስ) ከሃምሌ 01/2015 ዓ.ም ጀምሮ አክሲዮኖቹን ለህዝብ ክፍት በሆነ ገበያ አቅርቧል፡፡ የአክሲዮን ባለቤትነቱ ከብር ሃያ ሺህ የማያንስ እና ከብር ሁለት ሚሊዮን የማይበልጥ ነው፡፡

    ከተቋቋመበት ከ1984ዓ.ም ጀምሮ በመላ ሃገሪቱ በልዩ ልዩ የመሰረተ ልማት ግንባታ ስራ ተቋራጭነት ሲንቀሳቀስ ቆይቶ ከ አስራምስት ዓመታት በፊት በተጨማሪ ወደ ቤቶች ልማት ገበያ የተቀላቀለው ፍሊንትስቶን በትምህርት፣ በውሃ፣ በመብራት ሃይል፣ በመንገድ እና በመንግስት የቁጠባ ቤቶች ፕሮጀክቶች ላይ ግዙፍ አሻራዎችን አኑሯል። ወደ ሪልስቴት ከተቀላቀለ በኋላ ባሉት ያለፉት አስራ አምስት ዓመታትም በሺህ የሚቆጠሩ ደንበኞችን የቤት ባለቤቶች አድርጓል፣ በማድረግም ላይ ይገኛል።

    ዛሬ ላይ ደግሞ፣ ከሃገሪቱ ተስፋ የመነጨውን የድርጅቱን ራዕይ ዕውን ለማድረግ ፍሊንትስቶን ከእስካሁኑም እጅግ የላቀ ተልዕኮ ሊፈጽም ይገባዋል፡፡ በጥቂት ባለሃብቶች የሺዎችን ቤት ማቅረብ ከተቻለ ፣ ሺህ ሆኖ ደግሞ ለሚሊዮኖች እንኳን ቢከብድ፡ ለመቶ ሺህዎች የመኖሪያ እና መነገጃ ስፍራ ማዘጋጀት እንደሚቻል አያጠራጥርም፡፡

የግል ድርጅቶችን ለህዝብ ክፍት በሆነ ገበያ ማቅረብ ሁለት ቁልፍ እና ተመጋጋቢ ፋይዳ ያስገኛል፤

1ኛ. ከፍተኛ የገንዘብ እና የዕውቀት አቅም ያመጣል፣

2ኛ. ተጠያቂነትን እና ግልጽነትን በማስፈን መልካም የኮርፖሬት አስተዳደርን ( corporate good governance) ያሰፍናል፡፡

    ለሽያጭ የቀረበው አነስተኛ የአክሲዮን መጠን ብር 20ሺህ ከፍተኛው ደግሞ 2 ሚሊዮን የተደረገበትም አንዱ ምክንያት እነዚህ ሁለት ጣምራ ዓላማዎች ሊሳኩ የሚችሉት ብዙሃኑን ማሳመን እና ማርካት የሚችል ኩባንያ ከሆነ ብቻ እንዲሆን ለማድረግ ታቅዶ ነው። በርግጥ “ድርጅቱን እዚህ ደረጃ ያደረሱትን አመራር ቦታ የሚያሳጣ የአክሲዮን ግብይት መልሶ ድርጅቱን ለአደጋ አያጋልጠውም ወይ?” የሚል ሃሳብ ሊነሳ ይችላል ፣ ይህ ስጋት ተገቢ ቢሆንም በአመራሩ ብርታት በመተማመን በቅድምያ አክሲዮን የሚገዙት ብዙሃን በነባሩ ስንፍናም ሆነ በተተኪው አመራር አዲስ ሃሳብ ወይም ጉብዝና፣ በሂደት ብዙሃኑን የሚወክል አዲስ አመራር እያበጁለት እንደሚሄዱም ይገመታል። ለዚህም ነው ለብዙሃኑ ለሽያጭ የሚቀርብ የአክሲዮን ገበያ፣ ትውልድ የሚሻገር ኩባንያ ጠንካራ መሰረት ይሆናል ተብሎ የሚታሰበው። በአንድ ግለሰብ በ 6ሺህ ብር ካፒታል ተጀምሮ ዛሬ በቢሊዮኖች የሚቆጠር ስራን መስራት ከተቻለ በሺህ የሚቆጠሩ ባለአክሲዮኖች ገንዘብ እና በጎ አስተዳደር ምን ያህል ዘመን ተሻጋሪ ስራ እንደሚሰራ መገመት አያዳግትም ።

ሁሌም በለውጥ ሰዓት ለባለሃብቶች ሶስት ነገሮች የመሆን ዕድል ያጋጥማል፤ ቆዛሚም፣ አዝጋሚም፣ ተምዝግዛጊም መሆን ይቻላል፡፡ ተምዘግዛጊ መሆኑ ግን እጅጉን ያዋጣል፤ እንደንግድ ድርጅት፡፡ ሀገራችንን በጋራ፣ ሀብታችንን በአክስዮን እንገንባ፤

ፍሊንትስቶን ያንቺ ፣ ያንተ፣ የኛ

ለበለጠ መረጃ - 8188 ይደውሉ

Subscribe for updates

Subscribe for updates about Flintstone Homes, get notification for new offers and promotions.

Find us on Social Media