የፍሊንትስቶን ኢንጂነሪንግ አክሲዮን ማህበር የደንብና ሁኔታዎች አጭር መግለጫ  


1.

የፍሊንትስቶን ኢንጂነሪንግ አክሲዮን ማህበር አክዮኖች ሽያጭ በንግድ ህግ አዋጅ ቁጥር 1243/2013 እና በካፒታል ገበያ አዋጅ 1248/2013 መሰረት ነዉ፡፡


2.

የአክሲዮኖች ዋጋ
  • የአንድ መደበኛ አክሲዮን የተጻፈ ዋጋ (ፓር ቫልዩ) – 500 ብር
  • የአንድ መደበኛ አክሲዮን የዋጋ ብልጫ (ፕሪሚየም) – 250 ብር
  • መግዛት የሚቻለው ዝቅተኛ የመደበኛ አክሲዮን ብዛት - 40 አክሲዮኖች
  • መግዛት የሚቻለው ከፍተኛ የ መደበኛ አክሲዮን ብዛት - 4000 አክሲዮኖች

3.

የአክሲዮን ግዥ ክፍያ መፈጸም የሚቻለው በባንክ ወይም በፍሊንትስቶን ዲጂታል መተግበሪያዎች ብቻ ነው፡፡


4.

አክሲዮኖቹ ለማንኛውም ግለሰብ ህግን በተከተለ መልኩ መተላለፍ ይችላሉ።


5.

የአክሲዮኖች ሽያጭ የሚፈጸመው በአንድ ጊዜ ክፍያ ነው፡፡


6.

ባለአክሲዮኖች ክፍያቸውን እንዳጠናቀቁ የአክሲዮን ሰርተፍኬት ይሰጣቸዋል።


7.

ባለአክሲዮኖች አክሲዮኖችን በሙሉ ወይም በከፊል ወደቤት ግዥ ማዞር ይችላሉ።


በንግድ ህግ አዋጅ ቁጥር 1243/2013 እና በካፒታል ገበያ አዋጅ 1248/2013 መሰረት ደንብ እና ሁኔታዎች ተፈጻሚነት አላቸው።